XtGem Forum catalog
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

የአንብብ ትውልድ ሆይ! የድልህን ብስራት አንብብ!

✍ በወጣቱ ተልዕኮ(አህመድ የሱፍ)
Iqra

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ሙስሊሞች በኡኹድ ጦርነት ተሸንፈው በእጃቸው የነበረውን ድል ተነጥቀው ፣ ሽንፈትን ተከናንበው አዝነውና ተክዘው በተመለሱ ጊዜ አሏህ ሙዕሚኖች ድል የሚያደርጉበትን መንገድ እንዲህ ሲልነበር ያመላከታቸው።

አሏሁ አዘወጀል በቅዱስ ቃሉ በሱረቱል ኢምራን አንቀፅ 139 ላይ እንዲህ ይላል፦

=<({አል-ቁርአን 3:139})>=

{139} ደካሞች አትሁኑ፤ አትዘኑም። በእርግጥ እውነተኛ አማኞች ከሆናችሁ የበላዮች(አሸናፊዎች) ትሆናላችሁ።

ለምን ሶሃቦች(ረ.ዐ) አያዝኑ ፣ ለምንስ አይተክዙ ፣ ለምንስ አይደነግጡ? ምድር ላይ ካሉ ሰዎች ሁሉ በላይ ምርጥ የሆኑ 70 ሶሃቦች ያኔ ተገለዋል፤ ብዙዎች ተጎድተዋል ቆስለዋልም። የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ሳይቀሩ ፊታቸው በደም እስኪታጠብ ድረስ ቆስለዋል። በጭንቀት ላይ ሆነው ድክምክም እንዳሉ ጉንጮቻቸው ላይ ያለውን ደም እያበሱ በእርግጥ የመልዕክተኛውን ፊት በደም በለወሱት ሰዎች ላይ የአሏህ ቁጣ ብርቱና ከባድ ነው አሉ።

ነገርግን ይህ ሽንፈት ግዜያዊ መሰናክል ቢሆንም ሙዕሚኖች የሽንፈታቸውን ምክኒያት እንዲመረምሩ አስችሏቸዋል። የጥቂት ሙዕሚኖች ስህተት እና ሃጢያት የሙሉ ወታደሮችን ድል አስነጥቋቸዋል።

በኸሊፋዎች ዘመን ሙስሊሞች በማንኛውም ነገር የላቁና የተከበሩ ነበሩ። ታዲያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እኛ ሙስሊሞች መጥፎ ነገሮችን እየሰራን እና እያስፋፋን በመምጣታችን ፣ በማናውቀው ነገር ፈትዋ ለመስጠት በመቻኮላችን ፣ ከእምነታችን በላይ ገንዘብን ፣ ሃብትን ፣ ስልጣንን በመውደዳችን ፣ ከሰዎች ዘንድ ዝናንና ክብርን በመፈለጋችን ፣ የልዩነትን በር በመክፈታችን ያን ክብርን እና ታላቅነት አጥተን ዛሬ የማንም መጫወቻ ሁነናል።

ዛሬ በእኛ ላይ በሚዘምቱ ኩፋሮች ላይ መዝመት ቀርቶ ሙስሊሞች በሙስሊሞች ላይ መዝመት ጀምረናል። የሙስሊም ሃገራት እንኳ ሳይቀሩ ለአምስቱ ሃያል አገራቶች አጎብዳጅ ሁነዋል። በፓለስታይን ፣ በኢራቅ ፣ በአፍጋኒስታን ፣ በፓኪስታን ፣ በከሽሚር ፣ በበርማ ፣ በሊብያ ፣ በሶርያ እና በየመን የሚገደሉት ንፁሃን መስሊሞች እንደው ምን አድርገው ይሆን? የሰው ሃገር ወረው? በኩፋሮች ላይ በመዝመት ኩፋሮችን ጨፍጭፈው ነው? የሌሎች ሃገሮችን ድንበር ገፍተው ነው? ምን አድርገው ነው? ሌሎች ሙስሊም ሃገራቶችስ እነዚህን ሃገራቶች የሚወሩና ሙስሊሞችን የሚጨፈጭፍትን ለመታገል ምን አደርጉ? ምንም! የአቋም መግለጫ እንኳ አያወጡም! ታዲያ ሙዕተሲምን ምሳሌ አድርገው የሚከተሉ መሪዎች የታሉ?

ኡመር ኢብኑል ኸጧብ(ረ.ዐ) የሰአድ ቢን አቢወቃስ ወታደሮችን ወደ ቀድሲያ ጦርነት ሲልኩ ከጠላቶቻችሁ በላይ ወንጀላችሁ ለእናንተ አደገኛ ነውና ከጠላቶቻችሁ በላይ ወንጀላችሁን ፍሩ። እኛ ሙስሊሞች በጠላቶቻችን ላይ አሸናፊዎች የምንሆነው ሃጢያታቸው ከእኛ ሃጢያት በላይ በበዛ ጊዜ እንጅ በሌላ በምንም ምክኒያት አይደለም። ወንጀላችን ከጠላቶቻችን ወንጀል ጋር እኩል ከሆነ ያኔ በቁጥራቸው ብዛት ያሸንፉናል ሲሉ መከሩት።

ሰአድ(ረ.ዐ) ፐርዥያኖችን ለመዋጋት ሲነሳ የመሪውን ምክር ተግባራዊ ለማድረግ አስካሪ መጠጥ አዘውትሮ የሚጠጣውን ወታደሩን አቡ መህጃን(ረ.ዐ) ወደ ቤቱ ወስዶ አሰረው። አቡ መህጃህ እንደታሰረው የሰአድን ሚስት ልቧን የነካትን የግጥም ስንኝ ቋጠረ። ይህንም ስትሰማ ልቧ አልችል ብሏት ወንድሞቹጋ ጦርሜዳ ሄዶ እንዲሳተፍ ብላ ከታሰረበት በመፍታት የሰአድን ፈረስ አስይዛ ላከችው።

አቡ መህጃህ ጦርነቱን ተቀላቅሎ በሚገርም አኳኋን ተጋድሎ ከተመለሰ ብኋላ ተመልሶ ወደታሰረበት ይገባል። ሰአድ የዚህን ሰውየ ማንነት እስኪያውቅ ድረስ ለሶስት ቀን እንዲህ እያደረገ ቆየ። ሰአድ(ረ.ዐ) አቡ መህጃህ እንደሆነ ባወቀ ጊዜ የታሰረበትን ነገር ከፈታለት ቡኋላ በአሏህ ይሁንብኝ! ከዚህ ብኋላ አስካሪ መጠጥ በመጠጣትህ አላስርህም አለው። አቡ መህጃህም በአሏህ ይሁንብኝ! እኔም ከዚህ ብኋላ አስካሪ መጠጥ አልጠጣም ሲል መለሰለት። ወታደሮቹ ድልን ተጎናፅፈው፤ ሰልማኑል ፋሪስን(ረ.ዐ) የፐርዥያ አዲስ መሪ አድርገው ሹመው ተመለሱ።

ድል እና ሽንፈት ፣ ማግኘትና ማጣት ፣ ስኬትና ውድቀት በገንዘብ ፣ በሐብት ፣ በመሳሪያ ፣ በቁጥር ፣ በክህሎት አይወሰንም። ይልቁንም እነዚህ ነገሮች የሚወሰኑት አሏህን በመታዘዝ እና ባለመታዘዝ ሚዛን ነው። በተናጠልም ይሁን በግሩፕ የበለጠ አሏህን ስንታዘዝ አሏህ የበለጠ ወደ ድል ደጃፍ ያቀርበናል። አሏህ የበለጠ ባመፅን ቁጥር አሏህ ድልን ከእኛ ያርቅብናል። የአንድ ሙስሊም ወንጀል የብዙሃኖችን ድል ሊያዘገይ እንደሚችል እንወቅ። ጣታችነን ሌሎች ላይ ከመቀሰራችን በፊት እራሳችንን በደንብ እንመርምር!!!

ያ ኢኽወቲ ፊላህ! እስኪ ያለንበትን ሁኔታ እናስተውል! እራሳችነን እንፈትሽ! ሶላት የማንሰግድ ፣ ሲመቸን የምንሰግድ፤ ሲመቸን ደግሞ የምንተው ስንቶቻችን እንሆን? ዘካ ለመስጠት የምንሰስት ፣ አስካሪ መጠጥ የምንጠጣ ፣ ሐራም ነገሮችን የምንሸጥ ፣ የከንፈር ወዳጅ ያለኒካህ ያበጀን ፣ የምንሰርቅ ፣ የምናጭበረብር ፣ ሃራም ነገሮችን የምንበላና የምንጠጣ ፣ ዝሙት የምንሰራ ፣ መስጊድ አካባቢ ችግረኞች ተቀምጠው ገንዘባችነን በፋሽንና በቅንጦት ነገሮች ላይ የምናባክን ስንቶቻችን እንሆን?

ሙስሊሞች ሲታሰሩ ፣ ከሐገር ሲባረሩ ፣ ሲገደሉ ታዲያ ለምን እጃችነን መቀሰር አቃተን። ለምን ውዷ ጊዜያችነን የማይረባ ነገር እያየን እና እየተጫወትንስ እንደቀልድ እናሳልፋለን ።

ዛሬ ላይ ለሙዚቃና ለፊልም ከምንሰጠው ሰአት በላይ ለቁርአን አንድ ደቂቃ መስጠት ከብዶናል። ታዲያ ይህን ሁሉ እየሰራን የአሏህን ድል ከመጠበቅ ይልቅ የአሏህን ቁጣ እና ቅጣት መጠበቁ አይቀልም ትላላችሁ??

ወንጀሎችን በፈፀምን ቁጥር የሙስሊሞችን ድል እያዘገየን ነው። ከሃዲያኖች በዲናችን እንዲጫወቱ ፣ ቁርአንን እንዲያረክሱ ፣ ሙስሊሞች እንዲታሰሩና እንዲገደሉ ፣ የእህቶቻችን ክብር እንዲደፈር እየፈቀድን መሆኑን ልናውቅ ይገባል!!!

=<({አል-ቁርአን 3:139})>=

139 ደካሞች አትሁኑ፤ አትዘኑም። በእርግጥ እውነተኛ አማኞች ከሆናችሁ የበላዮች(አሸናፊዎች) ትሆናላችሁ።

አሏህ እረፍትን ፣ እርዳታን ፣ አሸናፊነትን ፣ የበላይነትን እና ድልን እንደሚያጎናፅፈን ቃል ገብቷል። መቼ? እውነተኛ አማኞች በሆን ጊዜ፤ እራሳችነን ለአሏህ ፍቃድ ሙሉ በሙሉ በማስገዛት በአሏህ መንገድ መታገል በጀመርን ጊዜ ነው!!!

1707

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ